Yohana – Hallo Lyrics

ዎሪያ ፥ ካሌ
ዎሪያ ፥ ካሌ

የሰው የለው ሞኝ (ዎሪያ)
የሰው የለው ሞኝ (ካሌ)
የሰው የለው ሞኝ (ዎሪያ)
የሰው የለው ሞኝ (ካሌ)
ካገሩ ከስፍራው (ዎሪያ)
ከቦታው ሲገኝ (ካሌ)
የሰው የለው ሞኝ (ዎሪያ ፥ ዎሪያ ፥ ዎሪያ ካሌ)

ላም አለቺኝ በሰማይ
ኖርኩኝ ወተቷን ሳላይ
ሳልመታ ለሷ መላ
ከእጄ አንቺን አጣሁ ሌላ

ያንቺ አልነበር እንደዋዛ
ጭንቅ እንጂ ችግር ቢበዛ
ሆድ ግን እንዳይብሰኝ አቦ
አጫውቺኝ በቀጭኑ ሽቦ

ሃሎ በይ ሃሎ ዲያስፖራ (ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ)
እንዳጠፊ እንደ ላሜቦራ (ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ)
ሃሎ በይ ሃሎ ዲያስፖራ (ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ)
እንዳጠፊ እንደ ላሜቦራ (ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ)
(ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ)

ትዝታሽን ደርድሬ (ድሬ-ድሬ)
ባይቀልልኝ ፍዳዋ (ዳዋ-ዳዋ)
ባትከብደኝ ውዬ አድሬ (ድሬ-ድሬ)
ቃልኪዳንሽ እዳዋ (ዳዋ-ዳዋ)

እፎይታ ሚያሳጣ አርባ (አርባ)
ቢኖር የሚያስብል ምን ጩህ (ምን ጩህ)
ከድምፅሽ ጉልበት ያርባ (ያርባ)
አይድረቅበት ምንጩ (ምንጩ)

በረሀ አንጥቶሽ እንደዋዛ
ሆነሻል ለሀገር ቤትሽ ወዟ
ሆድ ግን እንዳይብሰኝ አቦ
አጫውቺኝ በቀጭኑ ሽቦ

ሃሎ በይ ሃሎ ዲያስፖራ (ሃሎ ፡ ሃሎ)
እንዳጠፊ እንደ ላሜቦራ (ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ)
ሃሎ በይ ሃሎ ዲያስፖራ (ሃሎ ፡ ሃሎ ፡ ሃሎ)
እንዳጠፊ እንደ ላሜቦራ (ሃሎ ፡ ሃሎ)

የሰው የለው ሞኝ (ዎሪያ)
የሰው የለው ሞኝ (ካሌ)
የሰው የለው ሞኝ (ዎሪያ)
የሰው የለው ሞኝ (ካሌ)
ካገሩ ከስፍራው (ዎሪያ)
ከቦታው ሲገኝ (ካሌ)
የሰው የለው ሞኝ (ዎሪያ ፡ ዎሪያ ፡ ዎሪያ ፡ ዎሪያ ካሌ)

የሰው የለው ሞኝ
የሰው የለው ሞኝ
የሰው የለው ሞኝ
የሰው የለው ሞኝ
ካገሩ ከስፍራው
ከቦታው ሲገኝ
የሰው የለው ሞኝ

Comments (0)