ዮዮ አርገህዋል አላደረከውም
አርጌዋለውም ብልሽ አላረኩትም ብልሽ ያለፈ ነገር ነው አይደል? ማሬ
ቢያልፍም ማወቅ እፈልጋለሁ
ይሄውልሽ አሁን ሰላም ላይ ነው አ ያለነው ቤብ?
አንተነህ ሰላም የሆንከው እኔጋ ያለው ነገር ሰላም እየሰጠኝ አይደለም
ይሄውልሽ ባለፈ ነገር ሰላም አትጪ አልፈዋል
ለኔ አላለፈም እየዋሸኸኝ ነው?
ለምንድነው ምትጨቃጨቂኝ ዛሬ? አትጨቃጨቂኝ በቃ አልፈዋል
ጭቅጭቅ አይደለም እየተነጋገርን ነው ወይ አይ ወይ አው በለኝ
በግርግር አላዳፍነው ጠቅልዬ ፣ ጠቅልዬ
በንግግር አልግደልሽ ሙች ብዬ ፣ ሙች ብዬ
አይ አታርጊው ሌባና ፖሊስ ተይ ፖሊስ
አባሮሽ የቃል ይበቃል ፣ ይበቃል
የማርያም መንገድ ተይ መንገድ አዎ መንገድ
ስጪው ጠይቋል ፣ ጠይቋል ፣ ጠይቋል
አትሁኝ አጥብቆ ጠያቂ (ጠያቂ)
ሳትኖሪ የኖርኩትን ናቂ (ናቂ)
አትሁኝ አጥብቆ ጠያቂ (ጠያቂ)
ቆጥረሽ የቆረጥኩትን አታፋጪኝ
ባልሰማ እለፊ ባልሰማ ያለፈን ባልሰማ
ያላወቅሽውማ ያላየሽው የለም እያለሽ
ባልሰማ እለፊ ባልሰማ ያለፈን ባልሰማ
ያላወቅሽውማ ያላየሽው የለም እያለሽ
አታውጣጪኝ ፣ እነዳታመልጪኝ
ተይ አታውጣጪኝ ፣ በእጄ አታምልጪኝ
ድፍረት እንዳይመስልሽ ነው አፍሬ
ንቀትም አይደለም ነው አክብሬ
አፉ ብለሺኝ እለፊ እንጂ የዛሬን
ጫፉ ጥፋቴ ጎን አልገኝም ፍቅሬ
አይ አታርጊው ሌባና ፖሊስ ተይ ፖሊስ
አባሮሽ የቃል ይበቃል ፣ ይበቃል
የማርያም መንገድ ተይ መንገድ አዎ መንገድ
ስጪው ጠይቋል ፣ ጠይቋል ፣ ጠይቋል
አትሁኝ አጥብቆ ጠያቂ (ጠያቂ)
ሳትኖሪ የኖርኩትን ናቂ (ናቂ)
አትሁኝ አጥብቆ ጠያቂ (ጠያቂ)
ቆጥረሽ የቆረጥኩትን አታፋጪኝ
ባልሰማ እለፊ ባልሰማ ያለፈን ባልሰማ
ያላወቅሽውማ ያላየሽው የለም እያለሽ
ባልሰማ እለፊ ባልሰማ ያለፈን ባልሰማ
ያላወቅሽውማ ያላየሽው የለም እያለሽ
(ባልሰማ ፣ ባልሰማ ፣ በልሰማ) ተይ አታውጣጪኝ
(ያላወቅሽው ያላየሽው እያለሽ) እነዳታመልጪኝ
(ባልሰማ ፣ ባልሰማ ፣ በልሰማ) አታውጣጪኝ
(ያላወቅሽው ያላየሽው እያለሽ) ብቻ አታምልጪኝ
Comments (0)