አኸ አኸ ዘመዴ ነይ ነይ ያገሬ ልጅ
እስኪ ወዲያ ሄደሽ ወዲህ ተመለሺ
ለኛም ደስ ይበለን ሰዎቹም ይዩሺ
አላማጣ ውዬ መልሼ አላማጣ
በበሽታዬ ላይ በሽታ አላመጣ
ባንቻሮበ ገዳም በሶስቱ መንደር
እኔ የሽማግሌ ልጅ ተብዬ ነበር
ይኸው ባንተ በኩል ስሜ ሲሰበር
አንተ የምናምን ልጅ እኔን ሰው ያወቀኝ
እንዳልመጣ ኮራው እንዳልቀር ጨነቀኝ
እኮ
ሰብ ሰብ
እም አለምዬ
አኸ ኸ ዘመዴ
አንቺም ሰው ሆንሽና ሰው ቀጥሮ መጥፋት
እርሶም ሰው ሁነው ሰው ቀጥሮ መጥፋት
ደማደሞ ከንፈር አንቺ ዶዘር ፊት
ናናናና ናናአለምዬ
አልቻሜ ወልቻሜ የኔ ጥምር እግር
አንተ አለኸኝ ብዬ ለሰውም አልነግር
ሰብሰብ
አለም አለምዬ
አኸ ኸ ዘመዴ
እንካን አንቺንና ጥንብቻ ሆዷን
እንካን አንቺንና ጎተራ ሆዷን
ጥለናት መተናል የወይን ሀረጓን
እነይነይነይ
እም አለምዬ
አንተን ማን አረገህ የብርሌ ጠጅ
ግዜ ማሳለፊያ ቅራሬ ነህ እንጂ
ያንተ ያለህ ሰፕ
እም አለምዬ
አኸ ኸ ዘመዴ
ከንግዲስ ወዲያ አልለማመጥም
ጥርግ በል
ከንግዲስ ወዲያ አልለማመንም
እኔም አልፈልግም
እንደናዝሬት በርሜል ያንከባልሽ ማንም
Comments (0)