ክትክታና ወይራ ጥንጂቱ ነው ጢሴ
ጌጤን ድሬን አልሞቀው ሽብሽቦ ነው ልብሴ
ነጠላ ነው ልብሴ ሃገር ጠይቅብኝ
ይበርዳታል ብለህ እንዳትደርብብኝ
ይበርዳታል ብለህ እንዳትደርብብኝ
በቀጭኑ አልቦ ለተሰራው ልጅ
በቀጭኑ አልቦ ለተሰራው ልጅ
አሁን ምን ይገኛል ቢላክ አማላጅ
አሁን ምን ይገኛል ቢላክ አማላጅ
ጠይሙ ጎፈሬም ሸዋ ላይ ነው ቤቱ
ጠይሙ ጎፈሬም ሸዋ ላይ ነው ቤቱ
እኔ ባፈቅረውም አልሰጥ አሉ እናቱ
እኔ ባፈቅረውም አልሰጥ አሉ እናቱ
ክትክታና ወይራ ጥንጂቱ ነው ጢሴ
ጌጤን ድሬን አልሞቀው ሽብሽቦ ነው ልብሴ
ነጠላ ነው ልብሴ ሃገር ጠይቅብኝ
ይበርዳታል ብለህ እንዳትደርብብኝ
ይበርዳታል ብለህ እንዳትደርብብኝ
በትልቁ አዳራሽ አወጡት በማታ
በትልቁ አዳራሽ አወጡት በማታ
አይጫወትም ወይ በፋንታ በፋንታ
አይጫወትም ወይ በፋንታ በፋንታ
ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ጠፈጠፉ አራሰኝ
ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ጠፈጠፉ አራሰኝ
ፍቅርዬ ሆድዬ ኩታህን ጣልልኝ
ፍቅርዬ ሆድዬ ኩታህን ጣልልኝ
ክትክታና ወይራ ጥንጂቱ ነው ጢሴ
ጌጤን ድሬን አልሞቀው ሽብሽቦ ነው ልብሴ
ነጠላ ነው ልብሴ ሃገር ጠይቅብኝ
ይበርዳታል ብለህ እንዳትደርብብኝ
ይበርዳታል ብለህ እንዳትደርብብኝ
ይበርዳታል ብለህ እንዳትደርብብኝ
ይበርዳታል ብለህ
እንዳትደርብብኝ
ይበርዳታል ብለህ
እንዳትደርብብኝ
ኦ ኦ እንዳትደርብብኝ
ኦ ኦ እንዳትደርብብኝ
Comments (0)